=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ማንኛውም ሰው ህይወቱን በተለያየ መንገድ ያሳልፋል። ነገር ግን ወሳኙ ጥያቄ የህይወቱን ሃቅ የሞላ ወይም የፈፀመ ማነው? የሚለው ነው። እንስሳቶች የህይወታቸውን እያንዳንዷን ጊዜ እንዲሁ ያሳልፋሉ። ነገርግን ጊዜውን በጥበብ የተሰጠው የሰው ልጅ የተለያዩ ነገሮችን በመፈፀም ያሳልፋል።
ሆኖም ኩፋሮች የህይወታቸውን እያንዳንዷን ጊዜ ፅልመት በወረሰው ጠማማ መንገድ ላይ ሆነው ከቀጥተኛዋ የህይወት ጎዳና እንዳፈነገጡ....Read More
ፍቅር ማለት አንድን ነገር አብልጦ መውደድ ማለት ነው።
ሲጀመር አንድ ሰው በፍቅር ሊነደፍባቸው የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ አሏህ ፣ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፣ የአሏህ ባሮች ፣ እናት ፣ አባት ፣ እህት ፣ ወንድም ፣ ሚስት ወ.ዘ.ተ ነገር ግን ዛሬ ልዳስስ የምንፈልገው እኛ ወጣቶች ከሌላው በተለየ ስለሚያስደስተንና ስለሚፈትነን የፍቅር አይነት ነው። ማለቴ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ስላለን ግንኙነት በተመለከተ ነው።
ወጣቶችን ምርኮኛ የሚያደርጉ የዚህ ዘመን ወጥመዶች እና ፈተናዎች ከጊዜና ከቴክኖሎጅ መስፋፋት ጋር ተያይዞ እጅግ በጣም በርካታ ሆነዋል....Read more
በሽምግልና እድሜ የሚገኝ እውቀት ልክ በውሃ ላይ እንደሚፅፍ ሰው ሲሆን በወጣትነት ጊዜ የሚገኝ እውቀት ደግሞ ልክ በድንጋይ ላይ እንዳለ ማህተም ነው።
በወጣትነት እድሜ እውቀትን መሻት አስፈላጊ የሚያደርገው ነገር የጊዜ ጉዳይ ነው። እውቀትን መሻት አትኩሮት ፣ ድግግሞሽ የሚፈልግ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ምቹ ጊዜ የወጣትነት እድሜ ነው። ጊዜው ካለፈ በስራ መጠመድ ፣ ማግባት ፣ መውለድ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር ይኖራል። ይህ ደግሞ እውቀት የምንሻበትን ጊዜ ይቀንስብናል፤ ምናልባት ደግሞ....Read more
ሰዎች ለመዝናናት ፣ ለመሳቅ ፣ ለመጫወት ፣ ራሳቸውን ፈታ ለማድረግ ይረዱናል ብለው የሚያስቧቸው የመዝናኛ አይነቶች በሁለት ይከፈላሉ። አንዳንዶቹ በሃይማኖታችን የተከለከሉ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ የተፈቀዱ....Read more
ጓደኛህ ማን እንደሆነ ከነገርከኝ ማንነትህን እነግርሃለሁ!
መከራ ፣ ችግር አጋጥሞህ ጭንቀትህን ልታካፍለው አስበህ የነበረ ሰው የለም?
በጣም የሚወድህ ፣ ስትጨነቅ የሚጨነቅ ፣ ደስታህን ደስታው ያደረገ ጥብቅ ጓደኛስ ኖሮህ ያውቃል?
ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ እንድትጨነቅና እንድትተክዝ የሚያደርግህ ጓደኛስ አጋጥሞህ ያውቃል?
እኛ የሰው ልጆች ማህበራዊ ፍጡሮች እንደመሆናችን ጓደኞች እንዲኖሩን እንፈልጋለን። አብዛሃኛዎቻኛው የሂወታችን ክፍል ከሰዎች ጋር በመቀላቀል ወይም ማህበራዊ ትስስር ከመፍጠር ጋር የተያያዘ ነው....Read more
ሱብሃን አሏህ! ይህ የረሱል ኡማ ለጀሂልያው ዘመን ብርሃን የሆኑትን ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ካገኘ ቡኋላ ዳግም ወደ ጃሂልያ ዘመን መመለስን የሚሻ ይመስላል። በዚህም ላይ ልባችን የከዳን ወጣቶች በfacebook ላይ ያለን ተግባር(ፖስት የምናደርገው ፣ ላይክና ኮሜንት የምንሰጠው) ነገር ሁሉ ህያው ምስክር ነው። አጂብ ነው! 3ሰዓት ሙሉ facebook ላይ ነን ፖስት የምናደርገው ፣ ላይክና ኮሜንት የምንሰጠው እንዲሁም ቻት የምናደርግበት መሠረተ ሃሳብ ባዶ ነው። 3ሰዓት ሙሉ ለዲናችን ጊዜ የሰጠን ሙሉ 3ሰዓት ቁርአን በመቅራት ፣ ኢልምን በመሻት ጊዜያችንን የምናሳልፍ ስንቶቻችን እንሆን? ጊዜያችን እና ገንዘባችን እኛን መጥቀም ካልቻለ እኛም በሱ ላይ መጠቀም ካልቻልን ታዲያ መዳረሻችን ወዴት ሊሆን እንደሚችል አናስብም እንዴ? ስለዚህ ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ አይደለም ጊዜያችንን በእንቶፈንቶ....Read more
እውነትን መናገር በጣም የሚወደድ መልካም ልማድ ነው። ሁልጊዜም እውነትን የምንናገር ከሆነ እራሳችነን ከብዙ ችግሮች መጠበቅ እንችላለን። ይህ ብዙ መጥፎ ነገሮችን የሰራ ሰው ታሪክ ነው። ነገር ግን እውነትን ለመናገር ቃል በመግባቱ ከመጥፎ ነገር ጠብቆታል....Read more
ሸይጧን የጅኖች ወይም የአጋንት አንዱ አካል ሲሆን የራሳቸው የሆነ አለም ወይም መኖሪያ አላቸው። እራሳቸውን ከሰው ልጅ እይታ ከመሰወር ብቃት ጋር የተፈጠሩም ናቸው።
ሸይጧን እራሱን እንደ ሰው ልጆች ሁሉ የሚያበዛ ሲሆን የራሱ የሆኑም ዘሮች አሉት። አሏህ በሱረቱል ካኽፍ 18 : 50 ላይ እንዲህ ይላል:-
«መላኢካዎችንም ለአደም ስገዱ ባልን ጊዜ የነበረውን አስታውስ። ለአደም ስገዱ አልን ኢብሊስ ሲቀር ሰገዱ። ከጅኖችም መካከል ነበር። የጌታውንም ትእዕዛዝ አሻፈረኝ አለ። እናም ከኔ ይልቅ ሸይጧንና ዘሮቹ ጠላቶቻችሁ ሆነው እያለ ጠባቂና ረዳት አድርጋችሁ ትይዛላችሁን?»....Read more
በመልካም ነገር ማዘዝና ከመጥፎ ነገር መከልከል በኢስላም ትልቅ ሃላፊነት ሲሆን ኡለማዎች ይህን የተቀደሰ ተግባር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው ብለዋል። ምክርን እንለዋወጥ ዘንድ ሌሎችን መልካም ወደሆነ ነገር እናመላክት ዘንድ እና እርስበርሳችነም እውነት በሆነ ነገርና በትዕግስት አደራ አደራ እንባባል ዘንድ ታዘናል። ደህንነታችን የሚረጋገጠው በዚህ ላይ ሲሆን እሱን ችላ ማለት ደግሞ ውጤቱ የከፋ ነው....Read more
ለምንድነው እኛ ሙስሊም ወጣቶች ጓደኞቻችን ወደ አሏህ ቅርብ ይሆኑ ዘንድ የማንረዳቸው? በኢስላም ላይ ጥላቻ ያላቸው አስተማሪዎች ሶላታችነን እንዳንሰግድ ለማድረግ ከላይ ከታች ለሚሉ ሰዎች ፣ ሂጃብ ኋላቀርነትና ጭቆና ነው ለሚሉ ፣ በየሃይስኩሉ ፣ በየዩንቨርስቲው ላሉ ፀረ-ኢስላም አስተማሪዎች እና ፂማችነን ስላሳደግን የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱናን አጥብቀን ስለያዝን ስም ለሚለጥፉልን ሰዎች ሁሉ ቆምብለን ምላሽ ልንሰጣቸው ይገባል። እንዲሁም ሌሎች ለሚገጥሙን ፈተናዎች ሁሉ መልስ ለመስጠት እራሳችነን በእውቀት ፣ በጥበብ እና በማራኪ የአነጋገር ለዛ ልንክን....Read more
ዛሬ የብዙወቻችን ችግር ኢልም አይደለም ተግባሩ እንጂ። ብዙወቻችን አንብበናል ፣ ሰምተናል ፣ አውቀናልም ነገርግን ከአስተማሪውም ሆነ ከተማሪው የተግባር ሰው ጠፍቷል። መካሪው እና ተመካሪው እኩል....Read more
አሏህ በሰጠህ ተክለሰውነት ፣ አቇም ፣ ገንዘብ ፣ ልጅ ፣ ቤትና ችሎታ መብቃቃት ይኖርብሃል። የቁርአንም መልእክት ከዚህ የተለየ አይደለም።
=<({አል-ቁርአን 7:144})>=
44 የሰጠሁህንም ያዝ ፤ ከአመስጋኞችም ሁን....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|